የወራቤ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት
የወራቤ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ህንጻ
ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዝሃነት ውብ ተምሳሌት የሆነች ታላቅ ሀገር ናት። የተለያዩ ማንነቶች፣ እምነቶች፣ ባህሎች፣ ቋንቋዎችና የፖለቲካ አመለካከቶች በአንድነት የደመቁባት ሀገራችን፣ ልዩነቷን ወደ ጥንካሬና ውበት በመቀየር ለዘመናት በመከባበርና በመቻቻል የኖረች ናት። ዜጎቿም ውድ ሕይወታቸውን በመስዋዕትነት በመክፈል የሀገራቸውን ሉዓላዊነትና ነፃነት አስከብረው ለትውልድ አስረክበዋል።
ነገር ግን ከ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ጀምሮ የተፈጠሩ የተዛቡ ትረካዎችና የፖለቲካ አመለካከቶች ይህንን የጋራ እውነታችንን ለመሸርሸር ሞክረዋል። አንዳንድ ኃይሎችም አባቶቻችን የሀገር ምሰሶ ያደረጓቸውን እሴቶች የጥንካሬ ምንጭ ሳይሆን የድክመት ምንጭ ለማድረግ ሲሰሩ ቆይተዋል።የሀገራዊ ለውጡ ፈንጣቂ የሆነው የብልፅግና ፓርቲ ግን የሀገራችንን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ስብራቶች በዘላቂነት መፈወስ የሚቻለው በአገራዊ አንድነት፣ በወንድማማችነትና በእህትማማችነት መንፈስ ውስጥ ብቻ እንደሆነ በፅኑ ያምናል። ለዚህም ነው አገራዊ አንድነታችንን በሕግ፣ በአሠራርና በተቋም ደረጃ የትኩረታችን ማዕከል ያደረግነው።
በዚህ ታላቅ ጉዞ ውስጥ የወራቤ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት በከተማዋ ነዋሪዎች የተጣለበትን ታሪካዊ ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት ሌት ተቀን እየሰራ ይገኛል። ወራቤ ከተማ የስልጤ ሕዝብ መዲና፣ የሰላም፣ የአንድነትና የልማት ማዕከል እንደመሆኗ፣ በተለያዩ ዘርፎች የሚመዘገቡ ውጤቶች የከተማዋን ብሎም የሀገራችንን የብልፅግና ጉዞ ለማፋጠን የሚያበረክቱ ናቸው። ባለፉት ዓመታት በወራቤ ከተማ የሰላምና የመረጋጋት አየር በማጠናከር፣ የከተማ ልማትን በማስፋፋት፣ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገትን በማሳደግ እንዲሁም የሕዝብና የመንግስት ትስስርን በማጠናከር የሚታዩ ውጤቶችን አስመዝግበናል። የወራቤ ከተማ የብልፅግና አሻራም በተጨባጭ እየጎላ መጥቷል። እርግጥ ነው፣ በጉዟችን ላይ ፈተናዎችና ተግዳሮቶች አጋጥመውናል። ሆኖም እኛ ፈተናዎችን ወደ መልካም አጋጣሚ፣ አቅማችንን ወደ ላቀ ውጤት፣ ተግዳሮቶችንም ወደ ታላቅ ስኬት በመቀየር፣ በመተሳሰብና በወንድማማችነት እጅ ለእጅ ተያይዘን ውድ የሆነችውን ወራቤ ከተማን፣ የስልጤን ሕዝብና ታላቋን ኢትዮጵያ ከፍ ለማድረግ በፅናት ወደፊት ተጉዘናል፤ ጉዟችንንም እንቀጥላለን! በወራቤ ከተማ በየደረጃው የምትገኙ የፓርቲያችን አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች፣ እንዲሁም መላው የከተማችን ማህበረሰብ፤ የውስጥ አንድነታችንን ይበልጥ በማጠናከር፣ ድህነትን፣ ስንፍናን፣ ሌብነትንና ሙስናን በቆራጥነት በመታገል፣ የድካማችን ማማና የልፋታችን ውጤት የሆነውን ሁሉን አቀፍ ብልፅግና ማረጋገጥ የምንችለው በጋራ ትጋትና በተቀናጀ ተሳትፎ ነው። በዚህ ታሪካዊ ሂደት ውስጥ የወራቤ ከተማ ነዋሪዎች እንደ ሁልጊዜው የጽናታችን አለኝታና የጉዟችን ደጋፊ ሆናችሁ ከጎናችን እንደምትቆሙ ሙሉ እምነት አለን። በመጨረሻም፣ ለዴሞክራሲያችን መጎልበት የማይተካ ሚና ያላችሁ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ለወራቤ ከተማ፣ ለስልጤ ሕዝብና ለታላቋ ኢትዮጵያ ብልፅግና ሲባል በትብብርና በጋራ እንድንቆም ጥሪዬን አቀርባለሁ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነት፣ ፍቅርና ልፋት ትበለፅጋለች! አመሰግናለሁ!
አመሰግናለሁ!"
የወራቤ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ በርዕሰ መስተዳድር እንደሻው ጣሰው (ዶ/ር) ተመረቀ።
ወራቤ ግንቦት 14/2018ወራቤ ከተማ አስተዳደር ከ1.25 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸውን በርካታ የልማት ፕሮጀክቶችን በይፋ አስመርቋል።
የወራቤ የሀይል ማከፋፈያ ጣቢያ መንግስት የህዝብ ፍላጎቶችን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት ያለውን የላቀ ቁርጠኝነት ያረጋገጠበት መሆኑ ተገለጸ።