የፓርቲው መልእክት
![]() |
![]() የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አጭር መልዕክት አቶ ነስሬ አማን መሀመድ የወራቤ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊና ረዳት የመንግሥት ተጠሪ ዘርፋችን የከተማችንን ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞ በማሳለጥ ከተማችን የብልጽግና መዳረሻና የተሞክሮ ማዕከል እንድትሆን ጠንካራ የፖለቲካ አመራር በመስጠት በትጋት ይሠራል። “ከአዲስ ምዕራፍ፣ በወል እሴት ወደ መስፈንጠር ከፍታ” ብለን የጀመርነው የከተማችን የብልጽግና ጉዞ እውን እንዲሆን የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ የፖለቲካና የልማት ሥራዎች በስኬት እንዲተገበሩ ያስተባብራል። የከተማችንን ሁለንተናዊ ሁኔታ በመዳሰስ፣ የልማት ኢኒሼቲቮችንና የንቅናቄ ሥራዎችን በማስተባበር፣ የአመራርና የፓርቲ አባላትን የማስፈፀም አቅም በመገንባት፣ እንዲሁም የፓርቲያችንን እሳቤዎችና ገዥ ትርክት የመገንባት ትልም እውን እንዲሆን በትጋት ይሠራል። በአጠቃላይ ጠንካራ የፓርቲ ተቋም በመገንባት፣ ጠንካራ መንግሥትና የሀገረ መንግሥት በመገንባት ሂደት የወራቤ ከተማ ማህበረሰብ ግንባር ቀደም ተዋናይና ባለቤት እንዲሆን በማድረግ፣ ሰላማዊና የተረጋጋች ከተማ በመገንባት የፓርቲያችን የብልጽግና ህልምና ጉዞ እውን እንዲሆን አበክሮ ይሠራል። | ![]() የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አጭር መልዕክት አቶ ባህረዲን ሀሰን መሀመድ የወራቤ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊና ረዳት የመንግሥት ተጠሪ የፓርቲያችን የአደረጃጀት ዘርፍ በሀሳብ ትልቅነት ግዙፍ አባላትን፣ ሰፊ ቁጥር ያለውን አመራርና በተደራጀ የአሠራር ሥርዓት የሚመራ ጠንካራ የፓርቲ ተቋም ለመገንባት ይሠራል። የፓርቲያችን ህልም በመደመር መንገድ መዳረሻው ሁለንተናዊ ብልፅግናን በኢትዮጵያ በማረጋገጥ ለአፍሪካ ተምሳሌት መሆን ነው። ይህንን ታላቅ ሀሳብ ለማሳካት የፓርቲውን ግዙፍ አባላትና አመራር በተደራጀ፣ በተዓማኒነት ባለው መረጃና በተቀናጀ አሠራር መምራት ወሳኝ ነው። ስለሆነም፣ የወራቤ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ የብልፅግና ህልሙን እውን ለማድረግ በአደረጃጀት ዘርፍ የሚጠበቀውን ድርሻ ለማበርከት፣ በአግባቡ የተደራጀ፣ በዕቅድ የሚመራ፣ በፓርቲው እሳቤ አቅም ፈጥሮ የሚመራ፣ የፓርቲውን እሳቤ የሚከተል፣ በቋሚነት የሚወያይ፣ በተግባር አፈፃፀም የሚመዘንና የሚመዝን የብልፅግና ፓርቲ አባል፣ አመራርና አደረጃጀት መፍጠር ቀዳሚ ተግባሩ ነው። በአጠቃላይ፣ ብቁና ጠንካራ አደረጃጀትን፣ ተዓማኒነት ያለውን መረጃን እና በተግባር የሚፀና አባልና አመራርን በመገንባት የወራቤ ከተማ የብልፅግና ጉዞ እውን እንዲሆን በትጋት ይሠራል። ብቁና ጠንካራ አደረጃጀት፤ ተዓማኒነት ያለው መረጃ ለብልፅግና ስኬት!!! |
![]() | ![]() | ![]() |
![]() | ![]() | ![]() | ![]() | ![]() |










